# OSINT Post — @channel29news msg 46169

*Saturday, March 21, 2026 at 8:54 PM UTC — Hamer Intelligence Services Desk*

**Posted**: 2026-03-21T20:54:13.767Z (2mo ago)
**Fetched**: 2026-03-21T20:54:13.767Z (2mo ago)
**Views**: 10
**Media**: video
**Link**: https://t.me/Channel29News/46169
**Permalink**: https://hamerintel.com/data/posts/2225.md
**Source**: https://hamerintel.com/sources

---

#ICEየአሜሪካ ኢሚግሬሽንና ጉምሩክ ባለስልጣን (ICE) በይፋዊ የX ገጹ ላይ ያወጣው መረጃ መነጋገሪያ ሆኗል።ይኸው መረጃ ሰለሞን ቦጋለ የተባለ ኢትዮጵያዊ በሰብዓዊ መብት ጥሰት እና በዘር ማጥፋት ቅስቀሳ ምክንያት ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ስለመባረሩ የሚገልጽ ነው።ግለሰቡ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቹ ላይ ራሱን " የፋኖ አባል " አድርጎ መግለጹ ተጠቅሷል።በዚሁ መረጃ ላይ አሜሪካ "ፋኖ"ን በTier III (ምድብ 3) ሽብርተኛ ቡድንነት እንደፈረጀችው ተመላክቷል።ሰለሞን የተባለው ግለሰብም በትግራይ ተወላጆች ላይ " የዘር ማጽዳት " እንዲካሄድ እና ጥቃት እንዲሰነዘር በማህበራዊ ሚዲያ ሲቀሰቅስ ነበር ተብሏል።እነዚህን መረጃዎች ደብቆ ከአሜሪካ የኢሚግሬሽን ጥቅማጥቅሞችን ለመውሰድ በመሞከሩ ጥያቄው ውድቅ ተደርጎ ከሀገሪቱ ተባሯል።ግለሰቡ በአሪዞና፣ ፊኒክስ ባሉ የICE አባላት አማካኝነት እ.ኤ.አ መጋቢት 5 ተይዞ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ መደረጉ የICE መረጃ ገልጿል።ICE እ.ኤ.አ. ከ2003 ጀምሮ በጦር ወንጀል እና በሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚጠረጠሩ ወይም የተፈረደባቸውን 1,178 ግለሰቦችን ከአሜሪካ አባርሯል። ይህ " አሜሪካ እንዲህ አይነት ወንጀል የፈጸሙ ሰዎች መደበቂያ እንዳትሆን ለማድረግ የሚሰራው ስራ አካል ነው " ተብሏል። ለመሆኑ አሜሪካ " ፋኖን " አሸባሪ ቡድን ብላ በይፋ ፈርጃለች ?በICE የX ገጽ ላይ መረጃው ከወጣ በኃላ ከ100 ሺህ በላይ ሰዎች እይታ አግኝቷል ፥ 385 በላይ ሪፖስት ተደርጔል ፤ ከ1 ሺህ በላይ ላይክ ተደርጓል እንዲሁም በርካታ ሰዎች ከታች አስተያየት ሰጥተዋል።በርካቶቹ መነጋገሪያ ያደረጉት " ለመሆኑ መቼ ነው አሜሪካ ፋኖን በአሸባሪነ ቡድንነት የፈረጀችው ? Tier III ማለትስ ምን ማለት ነው ? " የሚለውን ነው።" Tier III " ምንድነው ? አሜሪካ የሽብር ቡድኖችን በ3 ዋና ዋና ምድቦች ትከፍላለች። እነዚህም ምድቦች እንደሚከተለው ተብራርተዋል።1. Tier I (ምድብ 1) በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በይፋ " Foreign Terrorist Organizations (FTO) " ተብለው የተፈረጁ ለምሳሌ፦ አል-ቃይዳ፣ አል-ሸባብ ፣ አይኤስአይኤስ፣ ታሊባን ሄዝቦላህ፣ ... አይነቶቹ ያሉበት ነው።2. Tier II (ምድብ 2)ይህ ዝርዝር ደግሞ ከምድብ 1 (በይፋ የታወጁ አሸባሪዎች) ዝቅ ያለ ሲሆን ዋና አላማው በዝርዝሩ ውስጥ የተካተቱ ድርጅቶች አባላት ወይም ደጋፊዎች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ የኢሚግሬሽን ቁጥጥር እና የቪዛ ክልከላን ለማድረግ ነው። 3. Tier III (ምድብ 3)እነዚህ " ያልተፈረጁ ወይም Undesignated " ቡድኖች ተብለው ነው የሚገለጹት። የአሜሪካ ኢሚግሬሽን ህግ ለኢሚግሬሽን ጉዳዮች እንደ ሽብር ቡድን ያያቸዋል።በአሜሪካ ህግ ትርጓሜ " በሽብር ተግባር ውስጥ የሚሳተፍ ወይም በሽብር ተግባር ውስጥ የሚሳተፍ ንዑስ ቡድን ያለው፤ የተደራጀ ቢሆንም ባይሆንም የሁለት ወይም ከዚያ በላይ ግለሰቦች ስብስብ " ተብሎ ይቀመጣል።Tier III (ምድብ 3) ድርጅቶች " በይፋ ያልተፈረጁ የሽብር ድርጅቶች/undesignated terrorist organizations " ተብለው የሚጠሩት እንደ ምድብ 1 እና ምድብ 2 ድርጅቶች ይፋዊ የመፈረጅ ሂደት ውስጥ ማለፍ ሳያስፈልጋቸው በሚያከናውኗቸው ተግባራት ብቻ እንደ ሽብር ቡድን ለመጠራት ብቁ ስለሚሆኑ ነው ይላል ህጉ።አንድ ቡድን እንደ Tier III (ምድብ 3) ሊቆጠር የሚችለው የኢሚግሬሽን ጥቅማጥቅም ጥያቄ በሚገመገምበት ወቅት ሲሆን እንደየጉዳዩ ሁኔታ የሚወሰን ነው። ምድብ 3 ውስጥ ያሉ አካላት በየጊዜው የሚፈጠሩ እና በሂደትም የሚለዋወጡ ናቸው።እስካሁን ባለው መረጃ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት "ፋኖ "ን በ "Foreign Terrorist Organization/ የውጭ አሸባሪ ድርጅት" ዝርዝር ውስጥ አላካተተም። ነገር ግን በTier III (ምድብ 3) ስር ከተካተቱ ቡድኖች ጋር ግንኙነት ያላቸው ወይም የደገፉ ግለሰቦች ወደ አሜሪካ ለመግባት ቪዛ ሲጠይቁ ወይም የጥገኝነት መብት ሲጠይቁ ለመከልከል እንደ ምክንያት ሊጠቀስባቸው እንደሚችል መረጃዎች ያሳያሉ።#ማጠቃለያ ፦ " Tier III (ምድብ 3) " በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መ/ቤት እንደ ምድብ አንድ በይፋ " የውጭ አሸባሪ ድርጅት (FTO) " ተብለው የሚፈረጁ አይደሉም። እነዚህ " በዝርዝር ውስጥ ያልሰፈሩ (Undesignated) " ነገር ግን በሽብር ተግባር ውስጥ የተሰማሩ ቡድኖችን የሚገልጽ የአሜሪካ ኢሚግሬሽን መጠሪያ ነው። Tikvah
